በመጨረሻው ቀን ማመን

ሙስሊም ሞት የህልውና ፍጻሜ ሳይሆን ከስራ ዓለም ወደ ዘላለማዊ ህይወት የሚደረግ ሽግግር እንደሆነ ያምናል፤ ይህችኛዋ ህይወት ለእያንዳንዱ ሰው እውነተኛው ጅማሬ ናት። ዘንጊዎች ሞትን እንደ መጨረሻ ሲያዩት፣ አማኙ ግን ከዱንያ ዝንጋቴ የሚቀሰቅስ እና ወደ ዘውታሪ ድሎት ወይም አሳማሚ ቅጣት የምታስቀድመው የበርዘኽ ህይወት መጀመሪያ መሆኑን ይገነዘባል። ይህም አማኙ በተውበት (ንስሐ)፣ በኢስቲግፋር (ምህረት በመለመን) እና የሰዎችን መብት በመመለስ ከአላህ ጋር ለመገናኘት ሁሌም ዝግጁ እንዲሆን ያደርገዋል።

የመጨረሻውን ቀን ማስታወስ የአማኝን ህይወት የሚቆጣጠር መሰረታዊ ማዕዘን ነው። የቀብር ስነ-ስርዓቶችንና መቃብሮችን ሲያይ የራሱም መጨረሻ ይኸው መሆኑን ያስታውሳል፤ ነገር ግን ተስፋ አይቆርጥም፤ ይልቁንም ጊዜው ከማለፉ በፊት እራሱን ይተሳሰባል። እውነተኛ አማኝ የመጨረሻውን ዓለም ማስታወስ አላህን በመታዘዝ ላይ ለመጽናት ትልቅ ረዳት ሆኖ ያገኘዋል፤ እንዲሁም የአላህን ውዴታ በመከጀል እና ልቦችና ዓይኖች በሚገለባበጡበት ቀን ከሚመጣው ቅጣቱ በመፍራት ኃጢአቶችን ከመፈጸም የሚከለክል ጠንካራ ገዢ ሆኖ ያገለግለዋል።

ሰዓቲቱ በቆመችና ሰዎች ከመቃብራቸው በተቀሰቀሱ ጊዜ፣ እያንዳንዱ ሰው በሞተበት ሁኔታ ላይ ሆኖ ይቀሰቀሳል። ከዚያም ሁሉም ለመሰብሰቢያው ቦታ ተነድተው በመለኮታዊ የፍትሕ ፍርድ ቤት ፊት ይቆማሉ። በዚያ አስቸጋሪ ቀን እያንዳንዱ ሰው ስራዎቹ በከፍተኛ ጥንቃቄ የተመዘገቡበትን መጽሐፉን ያነባል፤ በዚያ ቀን ዝናም ሆነ ገንዘብ ምንም አይፈይድም። ይልቁንም ስራው መልካም የነበረው ይድናል፤ ፍላጎቱን የተከተለና ጌታውን ያመጸ ደግሞ ይዋረዳል። እያንዳንዱ እንደ እምነቱና እንደ ስራው ፍዳውን ያገኛል።

በጀነት ውስጥ የአማኞች ደረጃ እንደ ቅንነታቸውና ጥረታቸው ይለያያል። ጀነት አላህ በዱንያ ላይ በእውነት ላይ ለታገሱ አላህን ፈሪዎች ያዘጋጃት ሀገር ናት። በክህደት ላይ የጸኑት ከሀዲያንና እምቢተኞች ደግሞ የዚህ ግትርነታቸው ዋጋ ይጠብቃቸዋል፤ በትንሳኤ ቀን ጸጸት በማይጠቅምበት ጊዜ የደረሰባቸውን ታላቅ ኪሳራ ይገነዘባሉ። ስለዚህ አማኙ የአላህን እዝነትና ምህረት ከሚከጅሉት ከቀኝ እጅ ባልደረቦች ለመሆን ይተጋል፤ ወደ ቁጣውና ቅጣቱ ከሚዳርጉ ነገሮች ሁሉ እራሱን ያርቃል።

يؤمن المسلم بأن الموت ليس نهاية الوجود، بل هو انتقال من دار العمل إلى حياة أبدية هي البداية الحقيقية لكل إنسان. فبينما يرى الغافلون الموت غايةً، يدرك المؤمن أنه يقظة من غفلة الدنيا، لتبدأ حياة البرزخ التي تسبق النعيم المقيم أو العذاب الأليم، مما يجعل المؤمن دائم الاستعداد للقاء الله بالتوبة والاستغفار ورد الحقوق لأهلها.

إن استحضار اليوم الآخر يُعدُّ ركناً أصيلاً يضبط حياة المؤمن؛ فهو يرى الجنائز والقبور فيتذكر أنها مصيره، لكنه لا يجزع بل يحاسب نفسه قبل فوات الأوان. فالمؤمن الصادق يجد في استذكار الآخرة عوناً على الصبر على الطاعات، ووازعاً قوياً يمنعه من ارتكاب المعاصي، طمعاً في رضا الله وخوفاً من عقابه يوم تتقلب فيه القلوب والأبصار.

عند قيام الساعة وبعث الناس من قبورهم، يُبعث كل امرئ على الحالة التي مات عليها، فيساق الجميع للحشر ليقفوا أمام محكمة العدل الإلهي. في ذلك اليوم العصيب، يقرأ كل إنسان كتابه الذي سُجلت فيه أعماله بدقة متناهية، ولا يغني فيه جاه ولا مال، بل ينجو من كان عمله صالحاً، ويذلُّ من اتبع هواه وعصى ربه، فلكل جزاؤه بحسب إيمانه وعمله.

تتفاوت منازل المؤمنين في الجنة بحسب إخلاصهم وجهادهم، وهي دار أعدها الله للمتقين الذين صبروا في الدنيا على الحق. أما المنكرون المعاندون فيلقون جزاء إصرارهم على الكفر، حيث يدركون يوم القيامة عظم الخسارة حين لا ينفع الندم. لذا، يسعى المؤمن ليكون من أصحاب اليمين الذين يرجون رحمة الله وعفوه، ويجتنب كل ما يؤدي إلى سخطه وعذابه.