ሶላት
ሶላት ሁለተኛው የእስልምና ማዕዘን እና የሃይማኖት ምሰሶ ነው። በቀንና በሌሊት አምስት ጊዜ ይሰገዳል፤ እነሱም ፈጅር፣ ዙህር፣ ዓስር፣ መግሪብ እና ዒሻ ናቸው። ሶላት ልብን ከአላህ ጋር የሚያገናኝ ድልድይ፣ ለነፍስ ንፅህና፣ እንዲሁም እምነትን የሚያለመልምና ከፈጣሪ ጋር ያለን ቃል ኪዳን የሚያድስ ዘውታሪ ውዳሴ ነው።
በእስልምና ሶላት እንዲሁ የተለመዱ የአካል እንቅስቃሴዎች ወይም ባዶ ስርዓቶች ብቻ አይደሉም። ከዚህ ይልቅ ልክ እንደ ሰውነት ነፍስ እንዳለው ሁሉ፣ የሶላትም ነፍሱ የአላህን ትዕዛዝ ለመፈጸም የሚደረግ እውነተኛ እምነት እና ጥርት ያለ ሃሳብ (ኒያ) ነው። ሶላት በባሪያና በፈጣሪው መካከል ያለ ቀጥተኛ ግንኙነት ነው። በዚህ ግንኙነት ወቅት ሰጋጁ ከማንኛውም ምድራዊ ፍላጎት ርቆና ልቡን ከይዩልኝ ስሜት አጥርቶ የአላህን ታላቅነትና ልቅና በመገንዘብ፣ ፍጹም ኃይሉን እያስታወሰ በፍራቻ በፊቱ ይቆማል።
ሶላት የዒባዳ (የአምልኮ) እና የማላቅ ከፍተኛው መገለጫ ነው። በአማኝ ልብ ውስጥ ለሞላው የተውሒድ (የአላህ አንድነት) እምነት ተግባራዊ መግለጫ ነው። አንድ ባሪያ ሩኩዕ (ሲያጎነብስ) እና ሱጁድ (ግንባሩን መሬት ላይ ሲያስነካ) ጥቅምም ሆነ ጉዳት በአላህ እጅ ብቻ መሆኑን እና ለዒባዳ እርሱ ብቻ ተገቢ መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ተግባር በሰጋጁ ነፍስ ውስጥ የ“አላሁ አክበር” (አላህ ታላቅ ነው) የሚለውን ትርጉም ያሰርጻል፤ ከፈጣሪው ታላቅነት አንጻር በዓይኑ ውስጥ ሁሉም ነገር ትንሽ ይሆናል።
የሶላት በአማኝ ህይወት ላይ ያለው በጎ ተጽዕኖ በባህሪው መቃናት ላይ ይንጸባረቃል። ሶላት እንዲሁ ውዳሴ ብቻ ሳትሆን፣ በንግግርም ሆነ በተግባር ለአላህ ታማኝ (ኢኽላስ) ለመሆን የሚሰጥ ቀጣይነት ያለው ስልጠና ነው። ትክክለኛ ሶላት አንድን ሰው ክልክል ከሆኑ ነገሮች እንዲርቅና ግዴታዎችን እንዲፈጽም ይመራዋል። እያንዳንዱ እርምጃውን የአላህን ውዴታ ብቻ ከመፈለግ ጋር እንዲያቆራኝ ያደርገዋል፤ ይህም ህይወቱን በሙሉ እምነቱን የሚጨምርና ነፍሱን ከፍ የሚያደርግ ተከታታይ ዒባዳ ያደርግለታል።
الصلاة هي الركن الثاني وعماد الدين، وتُؤدَّى خمس مرات في اليوم والليلة: الفجر والظهر والعصر والمغرب والعشاء. هي صلة القلب بالله، وطهارة للروح، وذكر دائم يُحيي الإيمان ويجدد العهد مع الخالق.
الصلاة في الإسلام ليست مجرد حركات جسدية أو طقوس جوفاء، بل هي جسد له روح هي العقيدة الصادقة والنية الخالصة لامتثال أمر الله. إنها صلة مباشرة بين العبد وخالقه، حيث يعترف المصلي بعظمة الله ومكانته، متجردًا من كل غاية دنيوية، ومنزهًا قلبه عن الرياء، ليقف بين يدي الله خاشعًا مستحضرًا لقدرته المطلقة.
تعد الصلاة أسمى مظاهر العبادة والتعظيم، فهي تعبير عملي عن عقيدة التوحيد التي يمتلئ بها قلب المؤمن. حين يركع العبد ويسجد، فإنه يؤكد أن النفع والضرر بيد الله وحده، وأنه المستحق وحده للعبادة. هذا الفعل يرسخ في نفس المصلي معنى "الله أكبر"، حيث يصغر في نظره كل شيء في جنب عظمة الخالق.
إن أثر الصلاة في حياة المؤمن يظهر في استقامة سلوكه، فهي ليست مجرد ذكر، بل هي تدريب مستمر على الإخلاص لله في القول والعمل. إن الصلاة الصحيحة تقود صاحبها إلى اجتناب المحرمات وامتثال الواجبات، وتجعله يربط كل خطواته بابتغاء رضا الله وحده، مما يجعل حياته كلها عبادة مستمرة تزيد إيمانه وتسمو بروحه.