ዘካ

ዘካ ሦስተኛው የእስልምና ማዕዘን ሲሆን፣ ከተወሰነ ንብረት ላይ የተወሰነ መጠን ለሚገባቸው ድሆችና ችግረኞች መስጠት ማለት ነው። ንብረትን የሚያጠራ፣ ነፍስን ከስስት የሚያጸዳ፣ በሙስሊሞች መካከል መረዳዳትንና ወንድማማችነትን የሚገነባ ግዴታ ነው።

በእስልምና ዘካ እንዲሁ የሚከፈል የገንዘብ ግብር ብቻ ሳይሆን ባሪያውን ወደ ጌታው የሚያቃርብ አምልኮ (ዒባዳ) እና የእምነትን እውነተኝነት በተግባር የሚያሳይ ሥርዓት ነው። በአላህ ውለታ የሚያምን ሙእሚን ገንዘቡ አላህ በእጁ ያስቀመጠለት አደራ መሆኑን ይረዳል። ስለዚህ ከዚህ ገንዘብ የተወሰነውን ክፍል ማውጣት መቀነስ ሳይሆን ነፍስን ከንፍገት ለማንጻት፣ ጸጋን በተግባር ለማመስገን እና ከቁሳዊ ፍቅር በላይ የፈጣሪን ፍቅር ለማሳየት ማረጋገጫ ነው።

ዘካ የእስልምናን ማህበረሰብ አንድነት ለማጠናከር ያለመ መሠረታዊ ማህበራዊ ምሰሶ ነው። በሀብታምና በድሃ መካከል የመተዛዘን ድልድይ ይገነባል፤ የወንድማማችነትና የመረዳዳት ስሜትንም ይዘራል። በዚህም የተነሳ ችግረኛው የችግሩን መፍትሔ ያገኛል፤ አቅም ያለው ደግሞ ከራስ ወዳድነቱ መውጣትን ይማራል። በዚህም ጥላቻ ይጠፋና መዋደድ ይሰፍናል፤ ማህበራዊ ግንኙነቶችም ከንፁህ ቁሳዊነት ተላቀው በአላህ እዝነትና የሁሉንም ባሮቹን ጥቅም በሚጠብቀው ህጉ ላይ የተመሠረቱ የላቁ ሰብዓዊ ግንኙነቶች ይሆናሉ።

አማኝ ዘካን ለመስጠት መቁረጡ ለአላህ ትዕዛዝ መታዘዙንና እርሱ በገባው የተተኪና የጭማሪ ቃል ኪዳን ላይ ያለውን እምነት ማሳያ ነው። እውነተኛ እምነት በሶላት ውስጥ በተዋረደ መልኩ እንደሚገለጸው ሁሉ፣ በዘካ ደግሞ በለጋስነት ይገለጻል። በዚህ አስተሳሰቡ ዘካ ለአማኙ የስነ-ልቦና ሚዛንን ይሰጠዋል፤ ከስግብግብነት ባርነት ነጻ ያወጣዋል፤ ልቡንም ከገንዘብ ይልቅ በአላህ ላይ እንዲንጠለጠል ያደርገዋል። እውነተኛ በረከት ለአላህ መንገድ በሚወጣው ነገር ውስጥ እንደሆነና እውነተኛው ሲሳይ (ሪዝቅ) ደግሞ ለመጪው ዓለም (አኺራ) የሚያስቀምጠው መሆኑን እንዲያረጋግጥ ያደርገዋል።

الزكاة هي الركن الثالث، وتعني أداء نسبة محددة من المال إلى مستحقيها من الفقراء والمحتاجين. هي فريضة تُطهِّر المال، وتُزكّي النفس من البخل، وتبني التكافل والأخوة بين المسلمين.

الزكاة في الإسلام ليست مجرد ضريبة مالية تُؤدى، بل هي عبادة تقرب العبد من ربه، وشعيرة تجسد صدق الإيمان بالعمل. فالمؤمن الذي يعترف بفضل الله عليه يدرك أن ماله أمانة استخلفه الله فيها، لذا فإن إخراج جزء من هذا المال ليس نقصاً فيه، بل هو تطهير للنفس من الشح، وتعبير عملي عن شكر النعمة، وبرهان على محبة الخالق فوق محبة المادة.

تُعد الزكاة ركناً اجتماعياً أصيلاً يهدف إلى تماسك المجتمع الإسلامي؛ فهي تبني جسوراً من التراحم بين الغني والفقير، وتغرس مشاعر الأخوة والتكافل. من خلالها يجد المحروم سداً لحاجته، ويتعلم الميسور كيف يتجاوز أنانيته، فيختفي الحقد وتنتشر المودة، وتتحول العلاقات الاجتماعية من مادية بحتة إلى علاقات إنسانية سامية قائمة على رحمة الله وشريعته التي تراعي مصالح جميع عباده.

إن التزام المؤمن بأداء الزكاة هو دليل على استجابته لأمر الله وثقته بوعده بالخلف والزيادة. فكما أن الإيمان الصادق يظهر في الصلاة خاشعاً، يظهر في الزكاة معطاءً. وهي بهذا المفهوم تمنح المؤمن توازناً نفسياً؛ إذ تحرره من عبودية الطمع، وتجعل قلبه معلقاً بالله لا بالمال، موقناً أن البركة فيما ينفقه في سبيله، وأن الرزق الحقيقي هو ما يدخره لآخرته.